Code 18
አንዳንድ ቀኖች በቀን መቁጠሪያ ላይ ብቻ የሚቀሩ ናቸው፤ አንዳንድ ቀኖች ግን የዓለምን ታሪክ ይቀይራሉ። ከእነዚህ ታላላቅ ቀኖች አንዱ ሐቢቡና ሙሐመድ ﷺ ወደዚህች ዓለም የመጡበት ቀን ነው።
ዓለም በጃሂሊያ ጨለማ ውስጥ ነበረች። ሰዎች በሽርክ ተዘፍቀው ነበር፤ ጠንካራው ደካማውን ይበድል ነበረ፤ ሴት ልጅ እንኳን እስከነሂወቷ የምትቀበርበት ዘመን ነበር።
በዚህ ጨለማ መካከል ግን አላህ አንድ ብርሃንን አመጣ፤ የመጨረሻው ነብይ፣ የሰው ልጆች መሪ፣ ሙሐመድን ﷺ።
አላህም እንዲህ አለ፦
﴿وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ﴾
“ለዓለማት ራህመት እንጂ አልላክንህም።”
ሀቢቡና ﷺ ራህመት ነበሩ፤ ቃላቸው ራህመት ነበር፤ ተግባራቸው ራህመት ነበር። የተበደለን ይረዱ ነበር፣ ለደካማው ይቆሙ ነበር፣ ለልጆች ርህሩህ ነበሩ፣ ለወጣቶች መልካም ምክር ይሰጡ ነበር። እንኳን በማያውቋቸው ሰዎች ላይ ያላቸው ርህራሄ የሚያስደንቅ ነበር።ለሰው ልጅ ያላቸው ክብር ገራሚ ነበር።
እሳቸው የመጡት አላህ በብቸኝነት እንዲመለክ፣ የሰው ልጅ ሕይወት ዋጋ እንዲኖረው፣ የደካማው መብት እንዲጠበቅ፣ ሴት ልጅ እንድትከበርና ፍትሕ እንዲሰፍን ነበር።
ለዚህም ነበር እኮ ኢብሊስ በመወለዳቸው በንዴት የተንገበገበው......እንዴትስ አይናደድ ለዘመናት የሰራው ሴራ መፍረሱን እያየ
{لَقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ}
ይህን አያ መስማቱ እንዴት ያስችለዋል???አለም ሁሉ በዚህ ታላቅ ሰው ሲመራ አለም በፍትህ ሲሞላ እነ አቡጃህልስ እንዴት መቻልን ያስቡ???! አጂጂጂብ
ሀቢቡና ለኛ ያላቸው ቦታ ይህ ነው ሚባል አይደለም ለዚህም ነው «ጠይቅ» በተባሉ ግዜ በዛች ቀን «ሸፈዓነቱን» ብለው የጠየቁት🥹
ፊዳካ አቢ ወኡሚ ያ ሃቢብ አላህ
✍ ሸይጣን ይደነግጥ፤ የዘመናችን አቡ ጃህሎችም ቀልባቸው ይፈራ ዘንዳ እኛም ሱናውን ሂያው ማድረጉን አንዘንጋ።
አላህ በመልካሙ ሁሉ ያግዘን
اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ

