ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከመካ ወደ ጣኢፍ ሲሄዱ ከመካ የተሻለ ነገር ይኖራል ብለው ነበር የሄዱት… — Suleyman Mehammed — TG.ME

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከመካ ወደ ጣኢፍ ሲሄዱ ከመካ የተሻለ ነገር ይኖራል ብለው ነበር የሄዱት ከሚደርስባቸው ግፍ መጠለያ ይሆናል ብለው ነው።

ሁሌ ሰው መማር ያለበት ብዬ እና እኔም በህይወቴ የተረዳሁት መልካም ያደርግልኛል ብለህ ያሰብከው ሰው ከጠበቅከው በተቃራኒ ሆኖ ያሳይሃል።
ጣኢፍ ላይ ካገኟቸው ሰዎች ውስጥ ከሶስቱ አንዱ የተናገረው ንግግር ሁሌም ይገርመኛል።

"አላህ ሰው አጥቶ ነው አንተን ነብይ አድርጐ የላከው?" ይህ ከባድ ልብ ሰባሪ ንግግር ነው ያግዘኛል ካልከው ሰው የተሰጠህ ምላሽ? በህይወትህ ምን ያህል ሰው በዚህ ልክ አስቀይሞሃል።

አስብ በአንተ የደረሰ ብቻ አይደለም በታላቁ ነብይም ደርሷል ሁሌም ቢሆን ጉዳይህ ወደ አላህ አዙር። ለሆነው ነገርም አትቀየም
👍6❤1
December 12, 2024 808 2