ከረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የህይወት ተሞኩሮ ሳንወጣ!
የአንድ ሰው የስኬቱ ሚስጥር ቤተሰቡ ደካማ ጐኑም ቤተሰቡ ናቸው።
በህይወትህ ውስጥ ትልቁ እገዛ ሚመጣው ከቤተሰብህ ነው ፤ በብዝሃነት ስንመለከት ረሱል የዚህ እድል ባለቤት በብዙ አልነበሩም የረሱል የህይወት ውጣ ውረድ በብዙ ነገር የታጠረ ነው።
አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ ሚስቱን ፣ አያቱን ፣ አባቱን ፣ እናቱን ፣ 6 ልጆቹን ወዳጆቹን አጥቶ በስተመጨረሻ አንድ ሚሳሳላት ልጁ የእርሱ መሞት ዜና በተሰማ በተወሰኑ ወራት ውስጥ እንደምትሞት ማወቅ ማለት ሀዘኑ ምን ያህል ነው በቦታው ሁናቹ አስቡት።
ይሄ ከባድ ፈተና ነው ይህንን ፈተና የደረሰበት ስንትሰው አለ ታድያ እኛ የከበደችን ትንሿ ፈተና ከነብዩ ጋ ሲነፃፃር ምን ድን ነው? ኢሄን ያደረገው አላህ ነው ሆኖም ግን ዳግም ወደ አላህ ይቀረቡ ነበር ታድያ የሁሉም አባት ሆኑ ፣ የሁሉም ሸፍዓ ሆኖ የአላህ ወዳጅ ሆኖ አንድ አንዴ በህይወት ምታጣው ነገር ትልቁን ደረጃ ለማግኝትም ይሆናል በትግስት ፅና።
3December 13, 2024 896 2