ወንድሞቼ መንገድ ያሳየን ሁሉ መንገድ ሊዘጋብን ነው ብለን አናስበ አጎራረስን የሚያሳይን ሰው ምግብን ሊቀማን… — Suleyman Mehammed — TG.ME

ወንድሞቼ መንገድ ያሳየን ሁሉ መንገድ ሊዘጋብን ነው ብለን አናስበ አጎራረስን የሚያሳይን ሰው ምግብን ሊቀማን እንዳይመስልን ማጉረስ የሚያጠግባቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ማመን አለብን።


ብዙ ክፉ ሰዎች ቢያጋጥሙን የሚያጋጥሙንን ሁሉ ክፉ አናድርግ ክፋታቸውን የማያውቁ ብዙ
ሰዎች አሉና ክፉ ነህ እያልን ክፋታቸውን አትቀስቅሱ።

ሰዎች ሁሉ ክፉ ናቸው ስልን ክፋታቸው እንወርሳለን ስለነሱ ብዙ ስናወራ ወሬው ታሪካቸው ያንቺ ያንተ እየሆነ ይሄዳል።

ደሞ ሌላው በቃኝ ልመጂ እጅሽ ከሞላ ይብቃሽ ወድቆ በነፃ ስላገኘሽ ብቻ ሆድሽን እጅሽን አትጠቅጠቂ በቃኝ ልመጂ እጅሽ ከሞላ ኪስሽ ከሞላ ዳር ላይ ማስቀመጥ ልመድ እጅህ እየሞላ አንድ እየጣልክ አንድ ስታነሳ
ከኖርክ ስግብግብ ትሆናለህ።

ወድቆ ያገኘሽው ነገር ሁሉ ያንቺ አይደለም እጅሽ ሲሞላ፣ ሆድህም ሲሞላ፣ ኪስሽ ሲሞላ የጎደለበትን አስብ ባዶ የሆነበትን አስቢ።


ከረጅም ታሪክ ላይ የተወሰደ
👍2❤1
September 3, 2024 1.4K 1