የአፋብን ፋይናንስ ኃላፊ እና የፖሊት ቢሮ አባሉ በለጠ አዱኛ ወልቃይት ጠገዴ ስቲት ሁመራ ዞን ሲደርስ በዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እና በመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች ደማቅ አቀባበል ተደረገለት‼
በለጠ አዱኛ እና አብረውት የገቡት የቀድሞ ታጣቂዎች የአማራን ሕዝብ ወሰን እና ማንነት ጥያቄ አሳልፈው ላለመስጠት የሰላም አማራጭን መከተላቸው ገለጹ።
በአማራ ሕዝብ የማንነት እና ወሰን ጥያቄ ስም የሚደረጉ የተሳሳቱ እንቅስቃሴዎችን በመቃወም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሕዝቡ መቀላቀላቸውን በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአፋብን ከፍተኛ መሪዎች ተናግረዋል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት በጫካ በተሳሳተ መንገድ መቆየታቸውን የጠቀሱት የአፋብን የፋይናንስና የሃብት ልማት ምክትል ኀላፊ በለጠ አዱኛ ወደ ጫካ የገቡት የሕዝብን ጥያቄዎች ለማስመለስ አልመው እንደነበር ጠቅሷል። ከዚህ አላማ በተቃራኒ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን እና የሕዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ አካሄድ በመኖሩ የመንግሥትን የሰላም አማራጭ መምረጣቸውን ገልጿል።
የእርስ በእርስ መገዳደል መፍትሔ እንደማያመጣ በመጠቆም ከመንግሥት ጋር በመኾን የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን አጋግጧል። ሌሎች ታጣቂዎችም ወደ ሰላም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ለታጣቂዎቹ አቀባበል ያደረጉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጌታቸው ሙሉጌታ እና የጠገዴ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ጋሻው ፍታለው የታጣቂዎቹን ውሳኔ አድንቀዋል።
መሪዎቹ በጫካ ያሉ አደረጃጀቶች የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈም ሀገር ለማፍረስ እየሠሩ መኾኑን ተረድተው ወደ ሰላማዊ መንገድ መመለስ ሀገርን እና ሕዝብን የሚያስቀድም ትክክለኛ ውሳኔ መኾኑን ገልጸዋል።
15
1




