ሰበር እና ጥብቅ መረጃ | "ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ እንዳይመጣ፤ ችግር ቢገጥመው እኛ አንጠየቅም!" - አቶ… — Mehal media — TG.ME

🚨 ሰበር እና ጥብቅ መረጃ | "ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ እንዳይመጣ፤ ችግር ቢገጥመው እኛ አንጠየቅም!" - አቶ አማኑኤል አሰፋ አደገኛ ዛቻ አሰሙ! 🚨

የህወሓት የጥፋት ቡድን የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ እና አደራዳሪ በሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ላይ ይፋዊ የደህንነት ማስጠንቀቂያ እና ዛቻ ማስተላለፉ ተጋለጠ።

ዛሬ ሐውልቲ አካባቢ በሚገኘው "የአርበኞች ጽ/ቤት" በተካሄደው የቡድኑ ስብሰባ ላይ አቶ አማኑኤል አሰፋ ያስተላለፉት መልዕክት፣ ቡድኑ ዲፕሎማቶችን አደጋ ላይ እስከመጣል የደረሰ አክራሪ አቋም መያዙን ያረጋግጣል።

📌 ከአቶ አማኑኤል አሰፋ የተሰነዘሩት አደገኛ ዛቻዎች እና ውንጀላዎች፦

* የጉዞ ክልከላ እና የደህንነት ማስፈራሪያ፦ አቶ አማኑኤል በግልጽ "ከዚህ በኋላ ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ እንዳይመጣብን፤ መጥቶ ችግር ቢገጥመው እኛ አንጠየቅም" በማለት፣ አደራዳሪው ትግራይ ውስጥ ቢረግጡ አደጋ ሊፈጸምባቸው እንደሚችል እና ለደህንነታቸው ኃላፊነት እንደማይወስዱ ዝተዋል።
* የፖለቲካ ውንጀላ፦ ኦባሳንጆ "ለብልጽግና ያዳላል" እንዲሁም "ለእኛ (ለትግራይ ህዝብ) ምንም የሚጠቅመው ነገር የለም" በማለት ሙሉ በሙሉ የሰላም እና የሽምግልና ሂደቱን ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
* የድሮን ጥቃት ክስ፦ ለዚህ ሁሉ ዛቻ እንደ ዋና መነሻ አድርገው ያቀረቡት፤ "የኦባሳንጆ ዋና ሀሳቡ ህወሓትን በድሮን ሊያስመታን ነው" የሚል እጅግ አስገራሚ እና የፈጠራ ክስ ነው።

ይህ የውስጥ መረጃ፣ ትላንትና የህወሓት ጽንፈኛ ክንፍ ኦባሳንጆን አልቀበልም ብሎ ካወጣው ይፋዊ መግለጫ ጋር በቀጥታ የሚገጣጠም ነው። አመራሮቹ የሰላም በሩን ከመዝጋት አልፈው፣ ዓለም አቀፍ የሰላም መልዕክተኞችን በአደባባይ በማስፈራራት ትግራይን ሙሉ በሙሉ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመነጠል እና ወደ አዲስ ጦርነት ለመክተት ቆርጠው ተነስተዋል።

#መሐልሚዲያ #MehalMedia #Mekelle #Obasanjo #Tigray #Ethiopia #AU #ሰበርመረጃ #Share
❤23👍2😁2💩1
September 7, 2026 3.4K 1