መሀል ሚዲያ የማበረታቻና የአድናቆት ሰርተፍኬት ተበረከተለት።
መሀል ሚዲያ በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ለሀገር መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ያሳየውን የሙያና የማኅበራዊ ድጋፍ በማድነቅ፣ ከጦር ኃይሎች ሆስፒታል የማበረታቻና የአድናቆት ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።
ሰርተፍኬቱ የተበረከተው መሀል ሚዲያ በተለይም ለሠራዊቱ አባላት የሚያደርገውን የማበረታቻና የአድናቆት ሥራ እውቅና ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል።
የጦር ኃይሎች ሆስፒታል ለመሀል ሚዲያ በሰጠው እውቅና መሀል ሚዲያ በበኩሉ ለሀገር ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉና በግዳጅ ላይ ለቆሰሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ያለውን አክብሮትና ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
🌐ለፈጣንና እውነተኛ መረጃ አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
✅መሀል ሚዲያ ቴሌግራም
https://t.me/mehalmedia
✅መሀል ሚዲያ ዩቲዩብ
https://youtube.com/@mehalmedia?si=qIrR-ugTjD0yFBJI
✅መሀል ሚዲያ ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1J3q2HKXKy/
✅መሀል ሚዲያ ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@desalegnmehal?_r=1&_t=ZS-93sj0dYufl2

14
12
4
2
1September 8, 2026 2.6K 1