መሐል ሚዲያ ከአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር አዲሱን የ2019 ዓ.ም ዓመት በደመቀ ሁኔታ አከበረ
መሐል ሚዲያ ለሀገር ውድ ዋጋ ከከፈሉ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመሆን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት መቀበያ በዓልን በጦር ኃይሎች ሆስፒታል በደመቀ ሁኔታ አክብሯል።
ዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም "የፅናት ቀን" ተብሎ በመላ ሀገሪቱ በሚከበርበት ዕለት በተካሄደው በዚህ ልዩ የደስታና የመዛመጃ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመከላከያ ጄኔራሎች፣ የመከላከያ የክብር አባላት፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በበዓሉ አከባበር ላይ እንደተገለጸው፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን በርካታ ፈተናዎችና ተፎካካሪ ሁኔታዎች ተቋቁማ ለዛሬዋ ከፍታ እንድትበቃ የሰራዊቱ አባላት የከፈሉት መስዋዕትነትና ያሳዩት ፅናት የማይተካ ሚና ተጫውቷል።
በዕለቱ የተከበረው "የፅናት ቀን"ም የሰራዊቱን የሀገር ፍቅር፣ ቁርጠኝነትና የነገን ብሩህ ተስፋ ይበልጥ የሚያጎላ መሆኑ ተስመሮበታል።
በዝግጅቱ ወቅት ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ያለው አክብሮትና ምስጋና የተገለጸ ሲሆን፣ መሐል ሚዲያም ከሀገር ጠባቂዎች ጎን በመቆም አዲሱን የ2019 ዓ.ም የሰላም፣ የልማትና የስኬት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
🌐ለፈጣንና እውነተኛ መረጃ አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
✅መሀል ሚዲያ ቴሌግራም
https://t.me/mehalmedia
✅መሀል ሚዲያ ዩቲዩብ
https://youtube.com/@mehalmedia?si=qIrR-ugTjD0yFBJI
✅መሀል ሚዲያ ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1J3q2HKXKy/
✅መሀል ሚዲያ ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@desalegnmehal?_r=1&_t=ZS-93sj0dYufl2
1
24
3
1
24
3
1September 8, 2026 2.6K 1


