ጥብቅ የውስጥ መረጃ | በራያ አላማጣ የህወሓት ሚሊሻ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በድብቅ ማስፈሩ ተጋለጠ! 🚨… — Mehal media — TG.ME

🚨 ጥብቅ የውስጥ መረጃ | በራያ አላማጣ የህወሓት ሚሊሻ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በድብቅ ማስፈሩ ተጋለጠ! 🚨

የህወሓት ታጣቂ ኃይል በራያ አላማጣ ወረዳ አዲስ የጦርነት ትንኮሳ ለመክፈት የሚያደርገውን አደገኛ ወታደራዊ ዝግጅት እና የከባድ መሳሪያ ስምሪት ሌሊቱን ማከናወኑን ታማኝ የውስጥ መረጃ ምንጮች አጋልጠዋል።

📌 ከስፍራው የደረሱን የወታደራዊ እንቅስቃሴ እውነታዎች፦

* 📍 የስምሪት ስፍራ፦ የከባድ መሳሪያዎቹ ዝውውር እና ምደባ የተካሄደው በራያ አላማጣ፣ ሓርሌ ቀበሌ ልዩ ቦታው ዓዲ በላይ ተላ በሚባል ጎጥ ውስጥ ነው።
* 📍 የመሳሪያው አቀማመጥ፦ የጥፋት ቡድኑ ሚሊሻዎች በጨለማ ሽፋን (ሌሊቱን) የጦር መሳሪያዎቹን በማጓጓዝ፣ በዚሁ ጎጥ ውስጥ በሚገኙ ሶስት የተለያዩ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ በድብቅ አከፋፍለው አስቀምጠዋል።
* 📍 የክትትል እና የማስጠንቀቂያ ጥሪ፦ ይህ ጽንፈኛ ኃይል አካባቢውን ዳግም ወደ ጦርነት ቀጠና ከመቀየሩ እና በህዝብ ላይ እልቂት ከመክፈቱ በፊት፣ የፌደራል መንግስት እና የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ይህንን እንቅስቃሴ በቅርበት በመከታተል አፋጣኝ እና ተገቢውን የቅድመ-መከላከል እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቀን እናሳስባለን።

📲 ይህ አደገኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለሚመለከታቸው አካላት ይደርስ ዘንድ አሁኑኑ ሼር (Share) በማድረግ ያጋሩ!

#መሐልሚዲያ #MehalMedia #RayaAlamata #Amhara #Tigray #Ethiopia #ጥብቅመረጃ #Share
❤21
September 7, 2026 3K