ሰበር እና ጥብቅ የውስጥ መረጃ | የነ ፈትለጽዮን ቡድን ቁስለኞችን እና ስንኩላንን ወደ አዲግራት እና አክሱም… — Mehal media — TG.ME

🚨 ሰበር እና ጥብቅ የውስጥ መረጃ | የነ ፈትለጽዮን ቡድን ቁስለኞችን እና ስንኩላንን ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች እያጓጓዘ መሆኑ በፎቶ ማስረጃ ተጋለጠ! 🚨
የጥፋት ቡድኑ (የነ ፈትለወርቅ እና ደብረጽዮን ስብስብ) በተለያዩ ካምፓሶች ተጠልለው የነበሩ የቆሰሉ እና አካለ-ስንኩል ታጣቂዎቹን ወደ ትምህርት ተቋማት (በተለይም ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች) በድብቅ እያጓጓዘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ተጨባጭ መረጃ እና የፎቶ ማስረጃ ለመሐል ሚዲያ ደርሷል።
📌 ከደረሰን መረጃ የተገኙ አበይት እውነታዎች፦
📍 የቁስለኞች ዝውውር ወደ ዩኒቨርሲቲዎች፦ የፈትለጽዮን ቡድን ለረጅም ጊዜ በተለያዩ ካምፓሶች ውስጥ ሲያሳክማቸው እና ሲጠልላቸው የነበሩ የጦርነት ቁስለኞች እና አካለ-ስንኩላንን ወደ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በስፋት እየወሰደ ይገኛል።
📍 የመለስ ካምፓሱ የፎቶ ማስረጃ፦ ከዚህ ጥብቅ መረጃ ጋር ተያይዞ የደረሰን (ከታች የሚታየው ፎቶ)፤ ቡድኑ በመለስ ካምፓስ ውስጥ የነበሩ ቁስለኞችን እና ስንኩላንን በመኪና ላይ ሲጭን እና ወደ አዲሶቹ የዩኒቨርሲቲ ካምፖች ሲያጓጉዝ የሚያሳይ መረጃ ነው።
(የመሐል ሚዲያ ማስታወሻ)፦ ቀደም ሲል ባቀረብነው ዘገባ የጥፋት ኃይሉ የቆሰሉ ታጣቂዎቹን (የፋኖ አባላትን ጨምሮ) ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ማስገባቱን ማጋለጣችን ይታወሳል። የትምህርት ተቋማትን ወደ ወታደራዊ እና የህክምና ማዕከልነት የመቀየር አደገኛ ስትራቴጂ ዩኒቨርሲቲዎቹን የጦርነት ቀጠና ከማድረግ ባለፈ ሌላ የሚያመጣው ፋይዳ የለም።
📲 የጥፋት ኃይሉን እኩይ ሴራ እና የትምህርት ተቋማት ወረራ ሁሉም እንዲያውቀው፤ መረጃውን አሁኑኑ ሼር (Share) በማድረግ ያጋሩ!
#መሐልሚዲያ #MehalMedia #AksumUniversity #AdigratUniversity #Tigray #Ethiopia #ሰበርመረጃ #Share
❤17
September 4, 2026 2.5K 3