ዳንግላ ከተማን ለማወክ የተንቀሳቀሱ የጽንፈኛ ቡድን 10 አባላት ተደመሰሱ
በዳንግላ አካባቢ ሰርጎ በመግባት የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ለማወክና የመንግሥትና የግል ንብረትን ለማውደም የተንቀሳቀሰ ጽንፈኛ ቡድን በመከላከያ ሠራዊት እርምጃ መደምሰሱ ተገለጸ።
የምሥራቅ ዕዝ ቃኝ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል ባሻ ገዛኸኝ እንደገለጹት፣ በተደረገው የጸረ-ሽምቅ ዘመቻ 10 የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ፣ 15 ሌሎች ቆስለዋል።
በዘመቻው አምስት ኤኬኤም መሣሪያዎች፣ ሁለት የቃታ መሣሪያዎች፣ አንድ ሽጉጥ፣ ሁለት የእጅ ቦንቦች፣ የወገብ ትጥቅ፣ የስናይፐርና የክላሽ ካዝናዎች ከተተኳሽ ጥይቶች ጋር መማረካቸው ተገልጿል።
ከተደመሰሱት ውስጥ በቡድኑ አጠራር የ44ኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ ኃላፊ የሚባል ግለሰብ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
የቃኝ ሬጅመንቱ ከአካባቢው የጸጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅና ነዋሪዎች ያለስጋት የዕለት ከዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችሉ የጸጥታ ኦፕሬሽኖች እንደሚጠናከሩ አዛዡ ገልጸዋል።

8September 1, 2026 1.5K