ሰበር ዜና ‼ በአገው አዊ ዞን ዳንግላን ለማወክ አቅዶ የመጣው ጽንፈኛ ቡድን እና በነሱ አጠራር የ 44ኛ… — Mehal media — TG.ME

#ሰበር ዜና

በአገው አዊ ዞን ዳንግላን ለማወክ አቅዶ የመጣው ጽንፈኛ ቡድን እና በነሱ አጠራር የ 44ኛ ክ/ጦር ዘመቻ ሀላፊው በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ተደመሰሰ።

በዳንግላ አካባቢ ጽንፈኛው ሰርጎ በመግባት ሰላማዊ ዜጎችን ለመግደል እና የመንግሥትና የግል ንብረት ለማውደም ቢንቀሳቀስም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ክንድ እርምጃ ተወስዶበታል።

በዚህ የፀረ-ሽምቅ ስምሪት 10 የጽንፈኛው ቡድን አባላት የተደመሰሱ ሲሆን 15ቱ ደግሞ ቆስለዋል። ፀረ ሰላም ኃይሉ ለጥፋት ተግባር ይጠቀምባቸው የነበሩ አምስት ኤኬ ኤም/ክላሽ፣ ሁለት የቃታ መሣሪያ፣ አንድ ሽጉጥ ፣ ሁለት የእጅ ቦንብ፣ የወገብ ትጥቅ፣ የስናይፐር እና የክላሽ ካዝና ከነተተኳሹ ተማርኳል።

ከተደመሰሱት ውስጥ በነሱ አጠራር የ44ኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ ኀላፊ ጭምር ተደምስሷል ።
❤28🙏9👍3
August 31, 2026 3.1K 1