የአሜሪካ የኃይል ሚዛን መሸርሸርና ያልተነካው የኢራን ከመሬት በታች የኒውክሌር ተቋም መገኘት ስጋት ደቀነ… — Mehal media — TG.ME

የአሜሪካ የኃይል ሚዛን መሸርሸርና ያልተነካው የኢራን ከመሬት በታች የኒውክሌር ተቋም መገኘት ስጋት ደቀነ

በኢራን ጦርነት ምክንያት ዋሽንግተን መዳከሟን ፑቲን ማመናቸውን የስለላ መረጃዎች ጠቆሙ

አሜሪካና እስራኤል ያካሄዱት ጥቃት የቴህራንን የኒውክሌር አቅም ሙሉ በሙሉ አላከሸፈውም ተባለ

በመካከለኛው ምስራቅ እያየለ የመጣውን ወታደራዊ ውጥረት ተከትሎ፣ አሜሪካ በጦርነቱ ምክንያት ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ አቅሟ መዳከሙን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ማመናቸውን የሚያመላክቱ የስለላ መረጃዎች ይፋ ሆኑ።

በሌላ በኩል፣ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ የሰነዘሩትን ጥቃት ተቋቁሞ ሙሉ በሙሉ ሳይነካ የቀረ ከመሬት በታች ያለ የኢራን የኒውክሌር ተቋም መገኘቱ ተገልጻል።

ዓለም አቀፉን የጂኦፖለቲካ የኃይል ሚዛን ሊቀይሩ የሚችሉትን እነዚህን ሁነቶች አስመልክቶ ብሪክስ ኒውስ እና ፎክስ ኒውስ  ባወጧቸው አዳዲስ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ግጭት የወለደው ውጤት ለዓለም አቀፍ ተፎካካሪ ኃይሎች አዲስ ስትራቴጂያዊ ዕድል ፈጥሯል።

የአሜሪካ የደህንነትና የስለላ ተቋማት ያወጧቸውን መረጃዎች ዋቢ በማድረግ የወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በኢራን ዙሪያ በገባችበት ረጅም ወታደራዊ ፍልሚያ ምክንያት ወታደራዊ አቅሟና የጦር መሳሪያ ክምችቷ መሸርሸሩን ገምግመዋል።

ዋሽንግተን ትኩረቷንና ሀብቷን ሙሉ በሙሉ ወደ መካከለኛው ምስራቅ በመስለኳ ምክንያት፣ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያላት የተጽዕኖ አቅም መዳከሙን ክሬምሊን እንደ መልካም አጋጣሚ መቁጠሩ ተጠቅሷል
❤9👍1
September 1, 2026 2.1K 1