🚨 አስቸኳይ ጥቆማ እና የሰራተኞች የቁጭት ድምጽ | በትግራይ ቴሌቪዥን በአድዋ ተወላጆች የተፈጸመው የጅምላ ማባረር ሴራ! 🚨
ከመቀሌ የመንግስት ሰራተኞች ዘንድ የደረሰን አስቸኳይ እና አሳሳቢ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና የትግራይ ቴሌቪዥን ኃላፊዎች በሆኑ አካላት መሪነት በሰላማዊ ሰራተኞች ላይ የጽዳት እና የማባረር ዘመቻ ተከፍቷል።
📌 ከተቀበልነው መረጃ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* 📍 የተሰበሰቡበት አዳራሽ እና ውሳኔ፦ በትግራይ ቴሌቪዥን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ፤ ህወሓትን የማይደግፉ፣ ጊዜያዊ መስተዳድሩን የሚደግፉ፣ የብልጽገና ደጋፊዎች እና የለውጥ ተከታይ የሆኑ ሰራተኞችን ከስራ ለማባረር ውሳኔ ተላልፏል።
* 📍 የኃላፊዎቹ ማንነት እና አድዋን መሰረት ያደረገ ማጣሪያ፦ ከስራ ለማባረር የተዘጋጁት ዋና ዋና ኃላፊዎች ሙሉ በሙሉ ከአድዋ የተውጣጡ ሲሆን፤ በዝርዝር የሰፈሩት ግለሰቦች፦
1. አባዲ ገብረስላሴ (ዋና ስራ አስኪያጅ - ከአድዋ)
2. ሊያ መስፍን (ቢዝነስ እና ፋይናንስ ምክትል ኃላፊ - ከአድዋ)
3. ተክለብርሃን (ፕሮሞሽን ኃላፊ - ከአድዋ)
4. የማነ ገብረሚካኤል (ዜና እና ትምህርታዊ ምክትል ስራ አስኪያጅ - ከአድዋ)
5. ገረዛሄር ሃይሉ (አማርኛ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር - ከአድዋ)
6. ክብሮም አብረሃ (ፖለቲካዊ ዳይሬክተር - ከአድዋ)
* 📍 የአድዋ ያልሆኑትን የማባረር ዘመቻ፦ እነዚህ ኃላፊዎች ከአድዋ ውጪ ያሉ ሰራተኞችን በመለየት "ህወሓትን አይደግፉም" በሚል ሰበብ ከስራ ለማፈናቀል እና ህይወታቸውን ለአስከፊ ችግር ለመዳረግ ጫፍ ደርሰዋል።
* 📍 የሰራተኞች የእርዳታ ጥሪ፦ "ጦርነቱ እና የባሰበት ችግር አልበቃ ብሎን አሁን ደግሞ ከኑሮአችን ሊያባርሩን ፈልገዋል" ያሉት የመቀሌ የመንግስት ሰራተኞች፤ ከስራ ተባረን አስከፊ ችግር ውስጥ ከመውደቃችን በፊት የፌደራሉ መንግስት እና የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ ሊደርስልን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
*(የመሐል ሚዲያ ማስታወሻ)*፦ የህዝብን መሠረታዊ መብት በመጥስ፣ የፖለቲካ ልዩነትን ምክንያት በማድረግ ሰራተኞችን ከስራ ማባረር እና ማሳደድ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ህገ-ወጥ ድርጊት ነው።
📲 ይህ አስቸኳይ የሰራተኞች የድምጽ ጥሪ ለሚመለከተው አካል ሁሉ ይደርስ ዘንድ፤ አሁኑኑ ሼር (Share) በማድረግ ያጋሩ!
#መሐልሚዲያ #MehalMedia #Tigray #Mekelle #Ethiopia #ሰበርመረጃ #Share

6September 1, 2026 1.5K