የጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ ሠራተኞች አድማ ሁለተኛ ቀኑን ያዘ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘው ጆሞ… — Mehal media — TG.ME

የጆሞ ኬንያታ አየር ማረፊያ ሠራተኞች አድማ ሁለተኛ ቀኑን ያዘ

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘው ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሠራተኞች የጀመሩት የሥራ ማቆም አድማ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል። በአድማው ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ መንገደኞች በበረራ መዘግየት እንግልት ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች ማኅበር (KAWU) እንደገለጸው፣ አድማው የተቀሰቀሰው በሠራተኞች በርካታ ቅሬታዎች ላይ መፍትሔ ባለመገኘቱ ነው።

ከዋና ቅሬታዎቹ መካከል ከኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጋር ስምምነት ላይ አለመደረሱ፣ እንዲሁም ከኬንያ አየር ማረፊያዎች ባለሥልጣን (KAA) እና ከኬንያ ኤርዌይስ እህት ኩባንያ ከሆነው ጃምቦጄት ጋር የትብብር እጥረት መኖሩን ማኅበሩ ጠቅሷል።

የኬንያ አየር ማረፊያዎች ባለሥልጣን እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ አንዳንድ በረራዎች መዘግየታቸውን ቢያስታውቅም፣ ለመዘግየቱ ምክንያት ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጠም። በኋላም በጉዳዩ ላይ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ እንዳልሰጠ ተገልጿል።

የኬንያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣንና ጃምቦጄትም በአድማው ላይ አስተያየት ከመስጠት መቆጠባቸው ታውቋል።
❤24
September 1, 2026 3.6K