ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የአገልግሎት ዘመናቸውን ላጠናቀቁት አምባሳደር ባጫ ደበሌ ሽኝት አደረጉ
******
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የአገልግሎት ዘመናቸውን አጠናቀው ለሚመለሱት በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ በናይሮቢ በሚገኘው ቤተ መንግስት ይፋዊ ሽኝት አድርገዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ በአሸኛኘት መርኃ ግብሩ ላይ፤ የሁለቱ ሀገራት፣ የመንግስታቱ እና የከፍተኛ አመራሩ የወደፊት ግንኙነት እና ወዳጅነት እጅግ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ባለፉት አራት ዓመታት የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልፀዋል።
የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር፣ የድንበር አካባቢ ደህንነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በሽኝት ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለአምባሳደር ባጫ ደበሌ ቀጣይ የስራ ዘመናቸው የስኬትን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
20September 2, 2026 2.2K





