የመኖሪያ ቤት ችግር በሞርጌጅ ባንክ ይፈታል የሚል እምነት የለኝም:: መሬቱ እንዳይታረስም ቤት እንዳይሠራበትም ጾሙን ውሎ እያደረ ባንክ ብቻውን ሊፈታው ቀርቶ ይብስ ይቆጣጥረዋል:: ምእመኑ በጊዜ ገደብ በጭቃ እንኳ ሠርቶ እንዲኖር አልተደረገም:: መሬቱ እንዳይሰምጥ ይሁን ወይም ጭቃው እንዳያስጠላ እንደሆነ ግልጽ አይደለም:: ከድህነትና እፍግ ብሎ ከመኖር በላይ ምን አስቀያሚ ነገር አለ? ያለፈው 20 ዓመት ያልተሠራበት ቦታ ዛሬም ሌጣ ሜዳ ነው:: ኑሮ እየተሻሻለ ሲመጣ ምእመኑ በራሱ እያሻሻለ ይሄዳል:: በእርግጥ በተለጠጠ ቁጥር መሠረተ ልማት ማሟላት አዳጋች ነው:: መንገድ ቀርቶ የውኃ መስመር መዘርጋት ፈታኝ ስለሆነ ፎቅ ላይ ማጠራቀም ዋጋ ይቀንሳል:: ፎቁስ የታለ? የምእመኑ ኢኮኖሚ ይፈቅዳል? ችግሩ ይህ ብቻ አይመስለኝም:: ገና የብሔ^ር ብሔ^ረሰብ ወሰን መች ተወሰነ? አዲስ አበባ ላይ ገና እየተጣላንማዴል!
ንብረት የማፍራት ዋስትና ቢከበር ኖሮ ብዙ ችግር ይቀረፍ ነበር:: አሁን ማን ደፍሮ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ንብረት የሚያፈራው? ቤት ከመሥራት መከራየት ባስመረጠበት ወቅት ... መከራየትም ነፍስ ውጪ ነፍ ግቢ በሆነበት በዚህ ጊዜ የቤት ችግር በቀላሉ ይፈታል ማለት አይቻልም:: የቱ ጋር መች እንደሚፈርስ መንግሥት ያውቀዋል? እልፍ ሲል ከደበረው በዚህ በኩል ቅደዱት, በዚህ በኩል እረሱት, በዚያ በኩል ይታደስ የሚባል ነው እኮ የሚመስለው:: የሆነ ሕጋዊ ቦታቸው ላይ ቤት በተገጣጣሚ ላሜራ የሠሩ ጎረቤቶቼ አሉ:: ድንገት ተነሱ አፍርሱ ከተባሉ እንዳይጨነቁ::
14
5
4
3
1September 6, 2026 1.7K