ከ500 ዓመታት በሗላ ዓለም የአፍሪካን "ትክክለኛ ካርታ" እንዲጠቀም UN መወሰኑ, ለምን አሁን ተወሰነ የሚለውን ትንታኔ የራሱ ጉዳይ:: ግን ይህንን ሁሉ ዓመታት መምህሩም ተማሪውም ውሸት መማርና ማስተማሩ ነው የሚገርመው:: ከወር በፊት የሆነ መምህር ይህንን ትክክለኛ የተባለውን አዲሱን ካርታ ቢያስተምር ኖሮ ከሥራ ሊባረር ይችል ነበር:: የፋይናንስ ሲስተሙ ደግሞ ከዚህ የባሰ ወጭበሬ ነው:: በብሩ ኒውዮርክ ውስጥ ምንም ዓይነት ዕቃ መግዛት የማይችል ምእመን በዶላር ግን አዲስ አበባ ውስጥ ሲገበያይ ለምን እንደማይጠይቅ አይታወቅም:: ይህንን ትክክለኛ የገንዘብ ምንነት ስናገር ስንቱ እንዳፈላብኝ እኔ ነኝ የማውቀው:: አንድ "ግድንግድ ኡስታዝ" የአሜሪካ ዶላር በኢትዮጵያ ብርም ይሁን በስዑዲ ሪያል መመንዘሩ ከሸሪዓ ጋር አይጋጭም:: ትክክለኛ ሥራ ነው:: ምክንያቱም ከለራቸው የተለያየ ስለሆነ እንደ ወርቅና እንደ ብር ቆጥረን መጠቀም እንችላለን ብሎ እኔን ለመቃወም መጽሓፍ ሁላ ጽፏል:: አሃሃሃሃሃሃ! ደረሶቹም አዎ ሸይኻችን ረጅም ዕድሜ ሲሉ ነበር:: ያው ሲስተሙ ሲሸከሽካቸው ግልብጥ ብለው መጡ እንጂ!
20
13
1September 6, 2026 1.8K 1