የንግድ ፈቃድ ካፒታል ስንት ቢሆን ይመከራል? -> በምትንቀሳቀሱበት ልክ አድርጉት:: ካነሰም መከራ ነው… — Hasen Injamo — TG.ME

የንግድ ፈቃድ ካፒታል ስንት ቢሆን ይመከራል?

-> በምትንቀሳቀሱበት ልክ አድርጉት:: ካነሰም መከራ ነው:: ከበዛም የባሰ መከራ ነው:: በ10 ሚሊዮን ብር እንቅስቃሴ የምታደርጉ ከሆነ በ1 ሚሊዮን ብር ካፒታል ንግድ ፈቃድ ብታወጡ ቀሪው ዘጠኙ ከየት መጣ የሚል ጥያቄ ያመጣል:: ከባንክ ብድር ከተሟላ መረጃ እስካለ ድረስ ችግር የለም:: ብድሩ ከግለሰብ ወይም ከራሳችሁ ከሆነ በውልና ማስረጃ የብድር ውል ብታካሂዱም ቅሉ ገቢዎች still ምንጩን ይጠይቃሉ:: ብድሩ ከራሳችሁ ከሆነ ድብቅ እንቅስቃሴ ወይም አደን^ዛዥ ዕ^ፅ እየሸጣችሁ ነው አይደለም በሚል ወደ ልዩ እና ሙሉ የባንክ አካውንት ኦዲት ይከታችሗል:: የቢዝነስ እና የግል የባንክ አካውንታችሁ ተለይቶ እየተንቀሳቀሳችሁ ቢሆን እንኳ ገቢዎች ድንበር ጥሶ ወደ ግል ሒሳብ ማጣሪያ ይገባል:: ብድሩ ከሌላ ሰው ከሆነ ከአራ^ጣ አበዳሪዎች ያመጣችሁት መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሌላ ገተት ውስጥ ትገባላችሁ:: የአበዳሪው ሒሳብ ወደ ማጣራት ይገባሉ:: ፈቃድ ስትጀምሩ ካበጠም ሌላ ችግር ነው:: ምክንያቱም ብሩን ማውጣት ይቸግራል:: ስለዚህ ፈቃድ ከማውጣታችሁ በፊት የእንቅስቃሴያችሁን ተመጣጣኝ ካፒታል ላይ አድርጉት::
❤28👍6😁1
September 6, 2026 1.8K 9