አፍላነት ሲሰክን
ቁዘማ ካበዛ፣
ልብ ቀልብ ከገዛ።
በይሉኝታ ሳይሆን በማስተዋል ጠፍር አምሮቱን ካሰረ ፣
ቀልድ አልጥምህ ካለው ነገር ካመረረ ።
ድንገት ዝ...ም ካለ 'ባሳብ ተጎትቶ፣
በደረቱ ኪስ ላይ ካዋለ እስኪሪብቶ።
ማድመጥ ከጀመረ ሀሳብ አስጨርሶ፣
መልበስ ከጀመረ ሱሪውን ተኩሶ።
በቃ እድሜውን ፈጀ፣
ወንድ ልጅ አ..ረ...ጀ !!
✍️ Zemed
@getmtg
@getmtg
7
2
1August 1, 2026 332 1 4