የሰፈራችን ጫካ ውስጥ ብቻውን ነው እንዴት እዛ ድረስ በራሱ እንደሄደ ገርሞኛል። ድክም ብሎታል እየመሸ ነው ተስፋ ግን አልቆረጠም። ወደ ሰፈር መመለስ አልፈለገም በችግር ውስጥ ሆኖ ማንም እንዲያየው አይፈልግም ። ቁስሉ የተመረዘበት ይመስላል ብዙ ደም ፈሶታል። ቸልተኛ ነገር ነው አይደለም ለሰውነቱ ለህይወቱም ግድ አይሰጠውም። ገና ከቀን ጀምሮ ስልኳ ላይ ይደውላል ይጠራል ግን አይነሳም ዋጋዋ የገባው ይመስለኛል። ለአመታት ጊዜ ሳይሰጣት ኖሮ የአንድ ቀን መስዋዕትነቱ ሊማርካት እንደማይችል ቢገባውም ገና በምናልባት ሊተዋት አልወደደም ።
በ 2005 ላይ ነበር እነሱ ሰፈር ተከራይታ የመጣችው ለሱ የተለየ ቀረቤታ ነበራት ።ከዛ ሁሉ የሰፈር ጎረምሳ እሱ ስቧታል ዛሬ ላይ ለምን ብትባል እንጃ ምናልባት እርጋታውና ቁምነገረኛነቱ የምትል ይመስለኛል ብትልም ደሞ አልተሳሳተችም ደሳለኝ የ 14 አመት ወዳጄ ነው በቅርበት አውቀዋለሁ በእድሜ በጣም ታናሼ ነው። እሷም አትነግረው እሱም አያምንላት እንዲሁ በአይን ፍቅር ሲቃጠሉ ቆይተው በተገናኙ በ 2ኛው አመት ወደ ፍቅር ገቡ።
በቃ ምን ልበላችሁ መልካም አፍቃሪ አይገልፃትም እሱ ግን ማን ጎሽ እንዳለው አይታወቅም ከቀን ወደ ቀን ኩራቱ እየባሰ ሄደ ያምርበታል'ኮ ግን ምንም ቢሆን ገደብ ያስፈልገዋል ። ግዜ አይሰጣትም ስልክ አይመልስላትም ብቻ ብዙ ብዙ ምናልባት የመጀመሪያው ስላልሆነች ይሆናል ። እሷም ከእለት እለት የሱ ፍላጎት ማጣት እረብሿታል መሰል ሁሉ ነገሯ ልውጥውጥ ብሏል። አንድ ቀን ቢጨንቃት መጥታ አማከረችኝ ተይው ማርቲ እሱ ለሁሉም ሰው እንዲህ ነው ደሞ የክፋት አይደለም ውስጡን ታውቂው የለ የዋህ ቢጤ ነው አልኳት ።
እንደ ማፈር ብላ ከሌላ ሴት ይሄድ እንደሆነ ጠየቀችኝ ሳሚ በፈጠረህ አትዋሸኝ አለች ። ምዬ እንደማያደገው ነገርኳት አመነችኝ ቻው ተባብለን ተለያየን ያን ቀን ማታ ሳስብበት አመሸሁ እሱ እንደሆነ ለማንም ግድ የለው ካንዴም ሶስቴ በሷ ጉዳይ ላወራው ሞክሬ በተቀመጥኩበት ነው ጥሎኝ የሄደው ስለዚህ ለምን እሷም ከምትጎዳ እኔም ብቻዬን ከማረጅ አናግሬያት አብረን አንሆንም ብዬ ወሰንሁ። በ ማግስቱም ስፈራ ስቸር ጠየቅኋት እሷም ለበቀል ነው መሰል በደስታ ተቀበለችኝ።
እሱም እንደለመደው አንድ ማታ ወደ ጎጆዬ ሳያንኳኳ ዘው ብሎ ገባ መርፌና ክር ሆነን .... አላመነም ሳሳሳሳ ሳሚ አንተ ከሀዲ ቆሻሻ ብሎ ጮኸ የራስህ ጥፋት ነው ምናባህ ጠብቀህ ነበር ብላ ጮኸችበት ። መልስም ሳይሰጥ አይኑ ላይ በገባለት ነገር ወርውሮ ሳተኝ ቡና መፍጫ ነበረ ። ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ምንም ደደብ ብሆን ወንድ ልጅ ነኝ ውሳኔዬ ቢሳሳትም ማንም እንዲረማመድበት አልፈልግም። በውስጥ ልብስ እንዳለሁ ከጓዳ ቢላ አፈፍ አድርጌ ወደሱ ተጠጋሁ እሱም በንዴት ነው መሰል ወደኔ ሲሮጥ ሆዱን ወጋሁት ። እሷ ደንግጣ ፍራሹ ላይ ቆማለች ግን ጨካኝ የሆነች መሰለኝ እንዴት ብትጠላው ነው? በሰላም መለያየት እየተቻለ።
ፍቅር ካለመስጠት ውጪ ምን አደረጋት? ....
✍️ Zemed
@getmtg
@getmtg
3
3
1
1June 1, 2026 689 1