:
አቅጄ ነበረ በልኬ ሰፍቼ
አጣማጅ አቻዬን ከ'ቅዴ ከትቼ
በውጣ ውረዴ በጎንበስ ቀናዬ
ነገን እያሳየሽ የቆምሽ ከኋላዬ
ነብስሽ እና ነብሴ አንዳች ሳይሞክሩ
እንደተላመዱ ምነው ቢፋቀሩ
ቀናት ሲጋልቡ ፣ አዝማናት ሲረግቡ
ጣፋጭ ቃሎቻችን ከጎታ ሳይገቡ
ልጆቻችን አድገው በወግ ሳያገቡ
ይሄን ሁሉ ሳላይ ፍፃሜ ትንቢቱን
ባንኜ ሳልነቃው የህልም ዓለም 'ሌቱን
እንዳላጣሽ ፈራሁ ያይኖቼን ማረፊያ
ወይ አላሳስርሽ እን ስርቆት ዝርፊያ
አልተክልሽም ነገር እንደ ደጅ አበቦች
ይዤሽ አልዞር ብትሆኝ እንደ ደሜ ስሮች
እና ምን ተሻለ፥
እንደው እንደ ዘበት እንደ አፍ ወለምታ
ሳይጨነቁበት እንዳስተጋቡት ቃል እንደ ቀን እፎይታ
ምነው ቢታከሙት አንቺጋራ መንተው የልብን ትርታ
እውነትን ተናገርሁ አምነሽ ተቀበይኝ
እኔ መሽቶብኛል አንቺም አሳድሪኝ።
✍️ Zemed
@ getmtg
@getmtg
8
2
1May 19, 2026 731 1 2