።።።።።
እኔ ምልሽ...
ታስታውሺ ይሆን ንገሪኝ እውነቱን
የህፃናት መዝሙር ያን እንኳን የጥንቱን
በዛ በበጋ(*2)
እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ...
አሁን አይደል የሚገባኝ..
ኑሮዬ ሳያንሰኝ ስቃዬን ልጨምር
ያመት ዕቅዴ ላይ"ፍቅር"የምደምር
ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ምስኪን ታዳጊ
በበጋ በሙቀት እጮኛ ፈላጊ
አይሰለቸኝ ቀኑ አያደክመኝ መንገድ
ላይዘልቅልኝ ነገር በልጅነት መውደድ
ስንከራተት ኖሬ..
ዘመን ጨላለመ ፀሀይዋም ጠለቀች
እድሜም አይገፋም ጨረቃ ግማሽ ነች።
አሁንስ ትዝ አለሽ...
መሸበትና ሰው ቤት ገባ
ልጅቷን አያት ተከናንባ🧕
በልብሽ ለማደር ሲመሻሽ ገባሁ
ተከልለሽ ባይሽ ልጠልፍሽ አደባሁ
ትዝ አለሽ ያ ደፋር...
እንደ'ንግድነቱ መከበር ሳያንሰው
ያሳዳሪውን ልብ የሚያስኮበልል ሰው
ደግሞ...
መውደድሽ ሳያንሰኝ ማሰቤ ሳይበቃ
የማስኮበልልሽ ለሊት በጨረቃ
እኔን የገረመኝ
በተከበርሽበት ሀገር እንዳትኖሪ፤
ባደግሽበት ደብር እንዳትቀበሪ፤
አምነሽ መከተልሽ ጨለማ ሳትፈሪ።
የ'ድላችን ማነስ
የኔ አንቺን ይዞ ዓባይ ድረስ መምጣት፤
ያባትሽ ርግማን የፈጣሪ ቅጣት፤
በበጋ ውሀ ሞልቶ መሻገርያ ማጣት።
ለካስ እኔ ነበርኩ ያ ግፈኛ ወጣት
ከቤቷ አስወጥቶ ለሒያጅ የሚሰጣት
በቆምኩበት የፍቅር ዕንባ እያለቀስኩ
ዕጣ'ድሌን እየረገምኩ እየወቀስኩ
ቀና ብዬ ሳያት ሙሉ ናት ጨረቃ
አንቺን ግማሽ ጎኗን ከ እጆቼ ነጥቃ
ምናይነት ገድ ነው?
የደረሰሽ ዕጣ የደረሰኝ ዕድል
ወንዝ'ንኳ ሲሞላ ፍቅር የሚያጎድል
ይኸው...
አንቺም የለሽ አትመጪም ተመልሰሽ
ወዶ መገፋቱ ቀድሞስ መች አነሰሽ
እኔም አለሁ...
ሌቱ አልበቃኝ ቀኑ ጉዟችንን ስስል
እኔና አንቺን ከመዝሙሩ ሳመሳስል
አንዲሁ ነን እኔና አንቺ...
መውደድ ውሉን ሳያሳጣን
ፍቅራችን ነው የሚያሰቀጣን።
በዛ በበጋ በዛ በበጋ......
7March 19, 2026 1K 6