በካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው የመኪና ዕድለኛ ሆነ
#FastMereja I በደቡብ ወሎ ኩታበር ወረዳ ነዋሪ የሆነው ወጣት ሰለሞን ብርሃን በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የቶምቦላ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆን የዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ባለቤት ሆኗል። በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው በርክከብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ወጣት ሰለሞን የመኪናውን ቁልፍ እና ህጋዊ ሊብሬ ተረክቧል።
በግል ካፌ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሠራው ወጣት ሰለሞን ብርሃን ከዕለት ተዕለት ሥራው በተጓዳኝ አዘውትሮ ሎተሪ የመግዛት የቆየ ልማድ እንደነበረው ገልጿል። ላለፉት በርካታ ዓመታት ተስፋ ሳይቆርጥ ዕድሉን ሲሞክር የቆየው ወጣቱ፣ አሁን ላይ የ3ኛ ዕጣ አሸናፊ በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማውና የዘመናት ትልቅ ሕልሙ እንደተሳካለት ተናግሯል።
ይህ በዕድል የደረሰውን ዘመናዊ ኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ለግል አገልግሎት ከመጠቀም ይልቅ ቀጣይ ሕይወቱን ለማሻሻል በሚያስችለው መልኩ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማሰማራት ማቀዱን ገልጿል።
7
2September 1, 2026 1.7K 3