በሚስ ወርልድ የሚሳተፈችው ሩት ይርጋለምን ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ህዝቡ ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ
#FastMereja I በ41ኛው የሚስ ወርልድ ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ በመሳተፍ ላይ የምትገኘው ሞዴል ሩት ይርጋለም በህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ከአፍሪካ በኤርትራ እና በናይጄሪያ ተበልጣ በሶስተኛ ደረጃ ላይ በመገኘቷ፣ እስካሁን የተሰጣት ድምፅ መና እንዳይቀር እና ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንድትሸጋገር ህዝቡ ድምፅ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚስ ወርልድ ናሽናል ዳይሬክተር ገነት ተስፋዬ ጥሪ አቀረቡ።
እንደ ናሽናል ዳይሬክተሯ ገለጻ ከሆነ፣ ተወዳዳሪዋ ሩት ይርጋለም በህዝብ ድምፅ አሰጣጥ ውድድሩን በሁለተኛ ደረጃ አጠናቃ ማለፍ ከቻለች በቀጥታ ወደ መጨረሻዎቹ 12 ተወዳዳሪዎች (Top 12) ውስጥ ለመግባት የምታደርገውን ጉዞ አስተማማኝ ያደርገዋል። በመቀጠልም ከ12ቱ የውድድሩ ምርጥ እጩዎች መካከል ወደ 6ቱ መጨረሻ ተወዳዳሪዎች የማለፉ ሂደት በራሷ የግል ብቃትና ዝግጅት የሚወሰን ይሆናል።
በመሆኑም እስካሁን የተካሄደው ድምፅ አሰጣጥና የተደረገው ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ፣ ተወዳዳሪዋ ያለችበትን የሶስተኛ ደረጃ አሻሽላ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ እንድትል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና ደጋፊዎቿ ድምፅ በመስጠት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ መልዕክት አስተላልፋለች።
13
5September 1, 2026 2.2K 1