በአንድ ነጥብ ልዩነት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡት እህትማማቾች ​#FastMereja I በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ… — FastMereja.com — TG.ME

በአንድ ነጥብ ልዩነት የላቀ ውጤት ያስመዘገቡት እህትማማቾች

​#FastMereja I በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ከተማ የሚኖሩት እህትማማቾቹ አሲያ ዲጋ ጂፋር እና አሚራ ዲጋ ጂፋር በዘመኑ የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ከአንድ ነጥብ ያነሰ እጅግ የተቀራረበ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተነገረ።

​በአዳባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረችው አሚራ ዲጋ 529.09 ያስመዘገበች ሲሆን፣ በአዳባ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረችው እህቷ አሲያ ዲጋ ደግሞ 528.58 በማምጣት በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት 0.51 ነጥብ ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል።

​ይህ በአንድ ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የተለዩ ትምህርት ቤቶች እየተማሩ የተመዘገበው ተመሳሳዩ ከፍተኛ ውጤት በአካባቢው ማህበረሰብ እና በትምህርት ባለሙያዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትን አትርፏል። ሁለቱ እህትማማቾች በጽናት ያደረጉት ጥረትና ውጤታቸው ለሌሎች ተማሪዎች ትልቅ ማበረታቻ መሆኑ ተገልጿል።
❤10
August 31, 2026 3.5K 2