ቲክቶከሯ ምህረት በጉራጌ የመስቀል በዓል አከባበርን ለማስተዋወቅ ተፈራረመች #FastMereja I የጉራጌ ዞን… — FastMereja.com — TG.ME

ቲክቶከሯ ምህረት በጉራጌ የመስቀል በዓል አከባበርን ለማስተዋወቅ ተፈራረመች

#FastMereja I የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ «ቪዚት ጉራጌ» እና ታዋቂዋ ተፅዕኖ ፈጣሪ ምህረት መስፍን (ምህሩ) የ2019 ዓ.ም የመስቀል በዓል አከባበር ባህልን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያለመ የታሪካዊ የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።

በወልቂጤ ከተማ በሚገኘው ጆካ ሆቴል በተካሄደው የምስራች ስነ-ስርዓት ላይ የዞኑና የከተማዋ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊዎች፣ የተፈጥሮ መስህብ ጥበቃና ልማት ቡድን፣ የኮሙኒኬሽን አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በተገኙበት ይፋ የተደረገው ይህ አጋርነት «የሚኖር ጉዞ» የተሰኘ አዲስ የቱሪዝም መርሀ ግብር ይዞ ቀርቧል።

ይህ ፕሮጀክት ወደ ጉራጌ ምድር የሚመጡ ሀገር ውስጥና የዲያስፖራ ጎብኚዎች በዓሉን ከሩቅ የሚያዩ እንግዳ ሳይሆኑ፣ የማህበረሰቡ አካል ሆነው የወጣቱን ጨዋታ፣ የደመቀውን ችቦ እና የእንግዳ ተቀባይነት ወግ እንደ ትክክለኛ ነዋሪ ሆነው እንዲለማመዱ እድል የሚፈጥር ነው።

ተሳታፊዎች ሙሉ ሰላምና ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ታላቁን የጉራጌ ባህል “ጀፎረ” በዩኔስኮ የማስመዝገብ ሒደት ተሳታፊ በመሆን በዓሉን በቅርበት እንዲያጣጥሙ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የዚሁ ልዩ መርሀ ግብር ተጋሪ እንዲሆኑ ጥሪውን አስተላልፏል።
❤23
August 30, 2026 4.9K