ግብፅ በናይል ውኃ ፍሰት ላይ መስተጓጎል ከተፈጠረ ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት አስታወቀች… — FastMereja.com — TG.ME

ግብፅ በናይል ውኃ ፍሰት ላይ መስተጓጎል ከተፈጠረ ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት አስታወቀች

​#FastMereja የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሀገራቸውን የውኃ ፍሰት የሚያስተጓጉል ማንኛውም ጉዳት ከተከሰተ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ራሳቸውን የመከላከል መብት እንዳላቸው ገለጹ።

ሚኒስትሩ የናይል ውኃ ለግብፅ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለ13 ዓመታት የተካሄደው ድርድር ያለ ምንም ስምምነት መዘጋቱን አስታውቀዋል።

​ቃለ መጠይቁ የተሰጠው በዚህ ሳምንት ከሃድሊ ጋምብል ጋር በተደረገ የቴሌቪዥን ውይይት ሲሆን፣ ሚኒስትሩ ግብፅ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌላትና ሕዝቡንም “ወንድሞችና እህቶቻችን” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

ሊወሰድ የሚችልን የወታደራዊ እርምጃ አማራጭ በተመለከተ በተነሳላቸው ጥያቄ፣ የግብፅ ጦር ዋና ተግባር ሀገሪቱን፣ ድንበሯንና ጥቅሟን ማስጠበቅ እንደሆነ አስረድተዋል። “ማንኛውንም አንድ ወገን ውሳኔ አንፈቅድም” ያሉት አብደላቲ፣ በውኃው ፍሰት ላይ መስተጓጎል ከደረሰ ግብፅ ሕጋዊ የመከላከል መብቷን እንደምትጠቀም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
👎17❤4😢1
August 29, 2026 4.9K 1