የትምህርት ሚኒስቴር በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር በ43.5 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነቡ ሦስት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን አስጀመረ።
------------------------- // ----------------------------
(ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የ2018 ዓ.ም ክረምት በጎ ፈቃድ በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን የሦስት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ያስጀመረ ሲሆን 4.3 ሚለየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍም አድርጓል።
በመርሃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮ፤ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፣የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ እና የቡኖ በደሌ ዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ ከ6ዓመት በፊት ያስጀመሩት ፕሮግራም ዛሬ ላይ ህብረተሰቡ ከቃል ወደ ተግባር ቀይሮታል ብለዋል።
ይህ መርሃ ግብር የህብረተሰባችንን የመደጋገፍ፣ የመተባበርና የመረዳዳት እሴት የበለጠ እንዲጎለብት አድርጎታል ያሉ ሲሆን፦
በዘንድሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ሦስት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሩንና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Jz8dB46Hx/
August 27, 2026 29.5K 14







