ማስታወቂያ በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ… — Ministry of Education Ethiopia — TG.ME

ማስታወቂያ
በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት በፌደራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ሙያ ለመቀጠር የተመዘገባችሁ እና ስማችሁ በዝርዝሩ ውስጥ ለተካተተ መምህራን የጽሁፍ ፈተናው ነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።
ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ፈተናው በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚቀርባችሁን በመምረጥ በአካል በመገኘት እንድትፈተኑ እናሳውቃለን፦
ፈተናው የሚሰጥባቸው ዩኒቨርስቲዎች፤
1. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
4. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
2. ወሎ ዩኒቨርሲቲ
5. ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ
8. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
3. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
6. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
9. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
   
 ማሳሰቢያ፣


1.   ለውድድር የተመዘገባችሁበትን መለያ ቁጥር (Reference Number) በመጠቀም የፈተና መግቢያ መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ማግኘት ትችላላችሁ፤
2.   በተጨማሪም መለያ ስም እና የይለፍ ቃል (Username & Password) ለፈተና በምትመጡበት ቀን በየዩኒቨርሲቲዎቹ ከሚመደቡ የፈተና አስተባባሪዎች ዘንድ ማግኘት ይቻላል፤
3.   ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
August 22, 2026 44.8K 46