ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው የኮምፒዊተር ኮዲንግ እና… — Ministry of Education Ethiopia — TG.ME

ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው የኮምፒዊተር ኮዲንግ እና አልጎሪዝም ስልጠና ተጠናቀቀ

---------------------------- // ------------------------

(ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ኮደር ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲስጥ የነበረው በኮምፒዊተር ኮዲንግ፣ ፓይተን ፕሮግራሚንግ እና አልጎሪዝም ላይ ያተኮረው የክረምት ሥልጠና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ።


በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ባስተላለፉት መልዕክት ሥልጠናው መንግሥት በሁሉም ዘርፍ ሀገራችንን ለማዘመን እየሰራ ያለውን ጥረት የሚደገፍ ወቅታዊና ተገቢነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።


ፕሮፌሰር ክንደያ አያይዘውም ሥልጠናው በተግባር የተደገፈ እና ተማሪዎች የማህበረሰብ ችግሮችን አጥንተው እንዲለዩና እንዲፈቱ ክህሎታቸውንና የፈጠራ ብቃታቸውን የሚያሳድግ መሆኑንም አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1eX8yGhVsA/
August 21, 2026 37.1K 34