ለተመረጡ የክላስተር ኮሌጅ የጋራ ኮርሶች አሰልጣኞች (TOT) ስልጠና ጀመረ።
ህዳር 12/2019 ዓ.ም. (DMPTC)
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ዘርፍ መልካም ስነ-ምግባር የታነፁ፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ቴክኖሎጂን በብቃት የሚጠቀሙ እና ሁለንተናዊ ብቃት ያዳበሩ ሰልጣኞችን ለማፍራት የሚያግዙ የጋራ ኮርሶችን በየኮሌጁ በተመሳሳይ ጥራት ለማሰጠት የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና (Training of Trainers - TOT) በደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተጀምሯል።
ስልጠናው በኢንተርፕረነርሺፕ (Entrepreneurship)፣ Human Edge Skills እና የሙያ ስነ-ምግባርና ስነ-ዜጋ (Professional Ethics and Civics) በተባሉ ሶስት የጋራ ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ክላስተር ኮሌጆች ለዚህ ዓላማ የተመረጡ አሰልጣኞች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ አሰልጣኞቹ በእነዚህ የጋራ ኮርሶች በቂ ዕውቀትና የማሰልጠን ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ፣ በየኮሌጃቸው ለሰልጣኞች ተመሳሳይ ጥራት ያለው ስልጠና እንዲሰጡ ማስቻል ነው። በዚህም ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ አቅም፣ የሙያ ስነ-ምግባር፣ የዜግነት እሴቶች እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ለስራ ገበያ የሚያስፈልጉ የHuman Edge Skills እንዲያዳብሩ ይረዳል።
ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደ ክላስተር ማዕከል በመሆን የአሰልጣኞችን አቅም በማጠናከር፣ በክላስተር ኮሌጆች መካከል የተቀናጀ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት እንዲጠናከር እና በአጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጥራት እንዲሻሻል የሚያግዙ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብሮችን በቀጣይነት እያከናወነ ይገኛል።
Debre Markos Poly Technic College
@dmtvet1990 · 1.1K subscribers
Educational channel ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉ https://telegram.me/dmtvet1990 ለበለጠ መረጃ ፌስቡክ ፔጃችንን ላይክ ያድርጉ https://m.facebook.com/Debre-Markos-Poly-Technic-College-531710730265642/?ref=opera_speed_dial share ያድርጉልን ለበለጠ መረጃ 0587711693 ይደውሉልን ድረገጽ www.dmptc.edu.et
Information
Username@dmtvet1990
Linkt.me/dmtvet1990
Channel history
We have been tracking it since August 9, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
These numbers aren’t from todayLast measured on October 18, 2026. The source has been silent since, so this is the last thing we saw — not the channel’s current state.
⌘K
Newest first
Share channel “Debre Markos Poly Technic College”
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/dmtvet1990Is this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →




















