ለተመረጡ የክላስተር ኮሌጅ የጋራ ኮርሶች አሰልጣኞች (TOT) ስልጠና ጀመረ።
ህዳር 12/2019 ዓ.ም. (DMPTC)
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ዘርፍ መልካም ስነ-ምግባር የታነፁ፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ቴክኖሎጂን በብቃት የሚጠቀሙ እና ሁለንተናዊ ብቃት ያዳበሩ ሰልጣኞችን ለማፍራት የሚያግዙ የጋራ ኮርሶችን በየኮሌጁ በተመሳሳይ ጥራት ለማሰጠት የሚያስችል የአሰልጣኞች ስልጠና (Training of Trainers - TOT) በደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተጀምሯል።
ስልጠናው በኢንተርፕረነርሺፕ (Entrepreneurship)፣ Human Edge Skills እና የሙያ ስነ-ምግባርና ስነ-ዜጋ (Professional Ethics and Civics) በተባሉ ሶስት የጋራ ኮርሶች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ክላስተር ኮሌጆች ለዚህ ዓላማ የተመረጡ አሰልጣኞች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ አሰልጣኞቹ በእነዚህ የጋራ ኮርሶች በቂ ዕውቀትና የማሰልጠን ክህሎት እንዲያገኙ በማድረግ፣ በየኮሌጃቸው ለሰልጣኞች ተመሳሳይ ጥራት ያለው ስልጠና እንዲሰጡ ማስቻል ነው። በዚህም ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ አቅም፣ የሙያ ስነ-ምግባር፣ የዜግነት እሴቶች እና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ለስራ ገበያ የሚያስፈልጉ የHuman Edge Skills እንዲያዳብሩ ይረዳል።
ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንደ ክላስተር ማዕከል በመሆን የአሰልጣኞችን አቅም በማጠናከር፣ በክላስተር ኮሌጆች መካከል የተቀናጀ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት እንዲጠናከር እና በአጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ጥራት እንዲሻሻል የሚያግዙ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብሮችን በቀጣይነት እያከናወነ ይገኛል።
1November 21, 2026 125 1



