ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴል ኢንዱስትሪ ለሚሰሩ ሰራተኞች የተግባር ስልጠና ጀመረ። ህዳር 12 ቀን…

ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴል ኢንዱስትሪ ለሚሰሩ ሰራተኞች የተግባር ስልጠና ጀመረ።

ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም /DMPTC/

ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በከተማዋ በሚገኙ የሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰሩ ሰራተኞችን ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ የተግባር ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ኮሌጁ ከሆቴል ባለቤቶችና አስተዳደሮች ጋር በመተባበር በሆቴል ዘርፉ የሚስተዋሉ የሙያ ክፍተቶችን በመለየት ለሰራተኞች ተግባራዊ የሆነ የአንድ ወር ተከታታይ ስልጠና አዘጋጅቷል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚሰጡ የሆቴል አገልግሎቶችን ጥራት ማሻሻል፣ ብቁና የተሻለ የሙያ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች ማፍራት እና የሆቴል ኢንዱስትሪውን ከተቋማት ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር ነው።

ይህ ስልጠና ከሆቴል ባለቤቶች ጋር በተደረገ የጋራ ውይይትና ስምምነት መሰረት የተጀመረ ሲሆን፣ ኮሌጁ ለኢንዱስትሪው ተግባራዊ የሙያ ልማት ድጋፍ በመስጠት ያለውን ሚና እያጠናከረ ይገኛል።
❤1👍1
November 21, 2026 68