ለደብረ ማርቆስ ክላስተር ኮሌጆች በመንግስት ግዥ አፈጻጸምና በንብረት አስተዳደር መመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
አርብ፡ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም (DMPTC)
በአዲሱ የመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 144/2018 ዓ.ም እና በመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 145/2018 ዓ.ም ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ለደብረ ማርቆስ ክላስተር ኮሌጆች ባለሙያዎች ተሰጠ።
ስልጠናውን ያዘጋጀው ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሆን፣ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የመጡ ባለሙያዎች ለደብረ ማርቆስ ክላስተር ኮሌጆች ተወካይ ባለሙያዎች ስልጠናውን ሰጥተዋል።
ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ይህ ስልጠና ዋና ትኩረት ያደረገው የመንግስት ግዥ አፈጻጸም ሂደትን፣ የንብረት አስተዳደር አሰራርን፣ የተጠያቂነት ስርዓትን እና የመመሪያዎቹን ትክክለኛ ተፈጻሚነት ማረጋገጥ ላይ ነው።
ስልጠናው በተቋማት ውስጥ የሃብት ብክነትን፣ የአሰራር ጥሰትን እና ከመመሪያ ውጭ የሚፈጠሩ ችግኝቶችን ለመከላከል በማገዝ፣ ግልጽ፣ ውጤታማና ተጠያቂ የሆነ የግዥና ንብረት አስተዳደር ስርዓት እንዲጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
Forwarded fromደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (DEBREMARKOS POLY TECHNIC COLLEGE)
November 20, 2026 185



