Global Entrepreneurship Week (GEW) ለአዲስ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች በግሩፕ የማማከር አገልግሎት በመስጠት ተከበረ።
ህዳር 11/2019 ዓ.ም (DMPTC)
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት (Global Entrepreneurship Week–GEW) በደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት ህዳር 11/2019 ዓ.ም ለአዲስ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች በግሩፕ የማማከር አገልግሎት ተሰጥቷል።
በመርሃ ግብሩ ወጣቶች የንግድ ሀሳባቸውን እንዴት ወደ ተግባራዊ ሥራ መቀየር እንደሚችሉ፣ የንግድ ዕቅድ አዘገጃጀት፣ የገበያ ጥናት፣ የፋይናንስ አስተዳደር፣ የቡድን ሥራ እና የንግድ ሥራ ተግዳሮቶችን በብቃት መቋቋም ላይ ሙያዊ ምክርና መመሪያ ተሰጥቷል።
ተሳታፊዎቹ ያሏቸውን የንግድ ሀሳቦች በቡድን በመወያየት ልምድ ተለዋውጠዋል፤ በባለሙያዎች የተሰጡ ምክሮችን በመቀበልም የንግድ ሥራቸውን ለማሳደግ የሚረዱ ግንዛቤዎችን አግኝተዋል።
ደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥራ ፈጠራ ባህልን በማጠናከር፣ ወጣቶችን ወደ ራስ ሥራ ፈጠራ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ተሳትፎ የሚያበቁ መርሃ ግብሮችን ከተባባሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በቀጣይነት ያከናውናል።
Forwarded fromደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ (DEBREMARKOS POLY TECHNIC COLLEGE)
November 20, 2026 203



