"ለበጎ ነው"
"አንድ ንጉሥ ከአጃቢው ጋር በመሆን ለአደን ይወጣል። ለአደን ሲወጡ ንጉሡ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው። በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉሥ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል። በዚህም ንጉሡ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት አስገባው።
ከብዙ ጊዜ በኋላ ንጉሡ ብቻውን ሀገሩን ሲዞር ሰው አርደው ለጣዖት መሰዋዕት የሚያደርጉ ጨካኝ ሰዎች ያዙትና አርደው መሰዋዕት ሊያደርጉት ሲሉ ቆራጣ እጁን አዩት። በእነሱ ህግ መሰዋዕት የሚያደርጉት ሰዉ ሙሉ ጤነኛ መሆን ስላለበት ለቀቁት።
ንጉሡ አጃቢው 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!' ያለው ትዝ አለውና እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩህ ይቅርታ አርግልኝ! ብሎ ታሪኩን አጫወተው። አጃቢውም "ማሰርህ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው። ንጉሡም "እንዴት?" አለው አጃቢውም "ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድና አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን ይገሉኝ ነበር" አለው።
ስለዚህ ሁላችንም ስለተደረገልንም ሆነ ስላልተደረገልን እንዲሁም ስለሆነውም ሆነ ስላልሆነው ነገር ሁሉ "ለበጎ ነው" ማለት ይልመድብን፡፡
240
43
7
6
3
3
2August 23, 2026 12.7K 176