በመስቀል ምልክት ሳታማትብ ከቤትህ አትውጣ፡፡ በትር፣ መሳሪያ፣ የማይበገር ምሽግም ይሆንሀል፡፡ ሰውም ሆነ… — ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ — TG.ME

በመስቀል ምልክት ሳታማትብ ከቤትህ አትውጣ፡፡ በትር፣ መሳሪያ፣ የማይበገር ምሽግም ይሆንሀል፡፡ ሰውም ሆነ ጋኔን አንተን ለማጥቃት አይደፍሩም፤ እንደዚህ ያለ ኃይለኛ የጦር ትጥቅ ታጥቀሃልና፡፡ ይህም አንተ ልክ እንደ ወታደር እንደሆንክ፣ ከአጋንንት ጋር ለመዋጋት ዝግጁ እንደሆንክ፣ በድልም አክሊልን እንደምታገኝ ምልክት ነው፡።

መስቀሉ ያደረገውን አታውቁምን? ሞትን አሸንፏል፣ ኃጢአትን አጥፍቷል፣ ሲኦልን ባዶ አድርጓል፣ ሰይጣንን ከዙፋን አውርዷል፣ አጽናፈ ዓለሙንም ወደ እግዚአብሔር መልሷል፡፡

ታዲያ ኃይሉን ትጠራጠራለህ? መስቀሉ ይህን ኹሉ ድንቅ ነገር አድርጎልናል፤ መስቀል በአጋንንት ፊት የቆመ የሽንፈታቸው መታሰቢያ ነው፤ ክርስቶስ እባቡን የገደለበት ሰይፍም ነው:: መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የአንድያ ልጁ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ውበት፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነው፡፡ ጳውሎስም እንዳለው መስቀል የቅዱሳን መከታ ነው፤ የዓለም ኹሉ ብርሃንም ነው፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅየነፍስ ምግብ ገጽ 78 በፍሉይ ዓለም የተተረጎመ)
❤135🙏37👍1
August 30, 2026 6K 65