ኢብኑል ቀይም አላህ ስለሚለው ስም ሲያወሱ
ይሄ ስም ትንሽ ነገር ላይ አይወሣም ቢያበዛው
እንጂ ፍራቻ ላይ አይወሣም ቢያስወግደው እንጂ
ጭንቅ ላይ አይወሣም ቢገልጠው እንጂ ደካማ
የሆነ ሰው አላህ ሚለውን ስም አያወሣም ሀይል
ቢሠጠው እንጂ የተዋረደ የሚባል ሠው በዚ ስም
ላይ አይንጠለጠልም ልቅናን ቢሠጠው እንጂ
ድሀ የሚባል ሠው በዚህ ስም ላይ አይንጠለጠልም
ቢያብቃቃውና ሀብታም ቢያደርገው እንጂ
አላህ የሚለው ስም❤ ችግሮች ሚወገዱበት በረካዎች
የሚወርዱበት ዱአዎች ተቀባይነት የሚያገኙበት ጥፋቶች
የሚቀሉበት መጥፎ ነገር ባጠቃላይ የሚገፈተሩበት መልካም
ነገር ሁሉ የሚመጣበት ሠማይና ምድር የቆሙት በዚህ ስም ነው
በሁሉም የሰው ልጆች ልብ ውስጥ የኔ አላህ የምትልን ቃል ያስቀመጠው የሠማይ ምድሩ ጌታ ሰማይ ምድርን የሞላ ምስጋና ይገባው ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ምርጥ በሆኑት መልዕክተኛ ላይ ይሁን ❤ መልካም ጁምዓ
October 26, 2026 97