ቁርአን ተሸፍኖ እንደሞተ አየሁ። እኔም አጠብኩት፣ ከፈንኩት፣ ከዚያም በላዩ ላይ የሟች ሰላት ሰገድኩበት። 📚…

ቁርአን ተሸፍኖ እንደሞተ አየሁ። እኔም አጠብኩት፣ ከፈንኩት፣ ከዚያም በላዩ ላይ የሟች ሰላት ሰገድኩበት።

📚 የኢማሙ አዝ-ዘሀቢይ (ረሒመሁላህ) «ሲየሩ አዕላሚ ን-ኑበላእ» በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ይላሉ፦

ከአንድ ቀን ጠዋት ወይም  ከሰዓታት በአንዱ፣ ከሊፋው አል-ሙዕተሲም በቁርአን ፍጡር ነው በሚለው የፈተና ዘመን በእስር ቤት ወደሚገኙት ወደ ኢማሙ አሕመድ ቢን ሐንበል መጡና፦

“አሕመድ ሆይ! እንዴት አደርክ?” አሏቸው።

ኢማሙ አሕመድም እንዲህ አሉ፦

“አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! ምስጋና ለአላህ ይገባውና በመልካም ሁኔታ አድሬያለሁ። ነገር ግን ያየሁት ሕልም አስጨንቆኛል፤ እስካሁንም ከአእምሮዬ አልወጣም። ”አሉት

ከሊፋው አል-ሙዕተሲምም፦

“ወዮልህ ያአሕመድ! ቁርአን ይሞታልን? ወይስ እያሾፍክብኝ ነው?” አሉ።

ኢማሙ አሕመድም እንዲህ አሉ፦

“ይህ የእናንተ ንግግር ነው፤ እናንተ ቁርአን ፍጡር ነው ትላላችሁ። እያንዳንዱ ፍጡር ደግሞ ይሞታል!”

ከዚያም ከሊፋው አል-ሙዕተሲም የዚያ ፈተና ዋነኛ አንቀሳቃሽ ከነበሩት ከኢብኑ አቢ ዱአድ ጋር ተመካከሩ። እሱም ለኸሊፋው እንዲህ አለው፦

“አሚረል ሙእሚኒን ሆይ! እኔ አህመድ በደንብ እንዲገረፍ እመክራለሁ፤ ከጅራፍ በስተቀር የሚያስተምረው ሌላ ነገር የለም!” አለ።

ከሊፋውም ኢማሙ አህመድን እንዲህ አላቸው፦

“አሕመድ ሆይ! ራስህን አታጥፋ፤ ቁርአን ፍጡር ነው በለኝና ከዚህ ቅጣት ዳን!” አሏቸው።

ኢማሙ አሕመድም፦

“ከመጽሐፉ ወይም ከመልእክተኛው ﷺ ሱና ከምትሉት ነገር የሚደግፍ ማስረጃ አምጡልኝ!” አሉ።

ከሊፋውም ለገራፊው፦

“ጅራፍህን አጥብቀህ ያዝና ግረፈው፤ ካልሆነ አላህ እጅህን ይቁረጠው!” አለው። ይህም ገራፊው በጠንካራ ሁኔታ እንዲገርፋቸው የተሰጠ ትእዛዝ ነበር።

ገራፊው የመጀመሪያውን ግርፋት ሲመታቸው ኢማሙ አህመድ፦

«بِسْمِ اللهِ»

“በአላህ ስም!” አሉ።

ሁለተኛውን ሲመታቸው፦

«لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ»

“ከአላህ ውጭ ምንም ኃይልና ብርታት የለም!” አሉ።

ሦስተኛውን ሲመታቸው፦

«الْقُرْآنُ كَلَامُ اللهِ غَيْرُ مَخْلُوقٍ»

“ቁርአን የአላህ ንግግር ነው፤ ፍጡር አይደለም!” አሉ።

ከዚያም ሌላ ግርፋት ሲመታቸው፦

«لَنْ يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللهُ لَنَا»

“አላህ ለእኛ የወሰነው ነገር እንጂ ሌላ ምንም አይደርስብንም!” አሉ።

ከዚያም ኢብኑ አቢ ዱአድ ወደ ኢማሙ አህመድ ቀረበና፦

“አሕመድ ሆይ! ከከሊፋው ቅጣት የሚያድንህን አንድ ቃል በጆሮዬ ሹክ በለኝ!” አለ።

ኢማሙ አሕመድም እንዲህ አሉት፦

“እንዴው አንተ  ወደ እኔ ቅረብና ከአላህ ቅጣት የሚያድንህን አንድ ቃል በጆሮህ ሹክ ልበልህ!” አሉት

ከዚያም ኢብኑ አቢ ዱአድ ገራፊውን ይበልጥ እንዲያሰቃያቸው ምልክት ሰጠው። ገራፊውም ኢማሙ አሕመድ ራሳቸውን እስኪስቱ ድረስ ይገርፋቸው ቀጠለ።

🌿 ከዚህ ታሪክ የምንወስደው ትምህርት፦

እውነት በችግር ጊዜ እንኳን መተው የሌለብን አደራ ነው። የሰዎች ቁጣ፣ ዛቻና ቅጣት የአላህን ቃል ከመከተል ሊያስቆሙን አይገባም። አንድ ሙእሚን በእውቀትና በማስረጃ ላይ ተመሥርቶ በእውነት ላይ መጽናት አለበት።

አላህ ኢማሙ አሕመድን ይዘንላቸው፤ በዲናቸው ላይ የነበራቸውን ጽናትም ለእኛ ትምህርት ያድርግልን።

اللَّهُمَّ ارْحَمِ الْإِمَامَ أَحْمَدَ بْنَ حَنْبَلٍ، وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ فِي الْمَهْدِيِّينَ، وَاجْزِهِ عَنِ الْإِسْلَامِ وَالْمُسْلِمِينَ خَيْرَ الْجَزَاءِ.

ኢላሒ...! ኢማሙ አሕመድ ቢን ሐንበልን ይዘንላቸው፣ በተመሩት ባሮቹ መካከል ደረጃቸውን ከፍ ያድርግላቸው፤ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ባበረከቱት አገልግሎትም ከሁሉ በላይ የሆነውን ምንዳ ይክፈላቸው።

📚 ምንጭ፦ ኢማሙ አዝ-ዘሀቢይ፣ سِيَرُ أَعْلَامِ النُّبَلَاءِ።
👍1
November 7, 2026 19