አል-ኢማሙ ሻፊኢይ ረሂመሁሏህ ሰው ማለት አራት አይነት ነው ይላሉ። 1.አዋቂ ነው ማወቁንም ያውቃል ይህ ሰው…

አል-ኢማሙ ሻፊኢይ ረሂመሁሏህ ሰው ማለት አራት አይነት ነው ይላሉ።

1.አዋቂ ነው ማወቁንም ያውቃል ይህ ሰው አሊም ነውና ተጠቀሙበት ይላሉ ።

2.ያውቃል ማወቁን ግን ዘንግቷል ይህን ሰው አስታውሱት ይላሉ ።

3.አያውቅም አለማወቁን ግን ያቃል ይህ ሰው መልካም ነገር ፈላጊ ነውና ምሩት ይላሉ።

4.አራተኛው አይነት ሰው አያውቅም አለማወቁንም አያቅም ይህ ሰው ጀህሉ ሙረከብ ነውና ራቁት ይላሉ

ለምን ሲባሉ ጃሂል እምቢ ብሎ ነው የሚረታህ ለዚህ ነው እኔ አሊምጋ ተወያይቼና ተከራክሬ አሸንፎኝ አያውቅም ጃሂል ግን እምቢ ብሎ ይረታኛል ይሉ ነበር አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው። ራሳችንን እንፈትሽ እኛ ከአራቱ የትኛው ላይ ነን?
October 25, 2026 84