ሐምዛ አል-አዕማ እንዲህ ብሏል፦
“ሐሰን አል-በስሪን ልጎበኛቸው በሄድኩ ቁጥር ሲያለቅሱ ነው የማገኛቸው። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሶላት ላይ ሆነው ሲያለቅሱ ያጋጥሙኛል።
አንድ ዕለት ታዲያ፦
“ ለምንድነው በጣም የሚያለቅሱት?” አልኳቸው።
እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ
“አይ ልጄ! አማኝ የሆነ ሰው ካላለቀሰ ታዲያ ምንድን ነው የሚያደርገው? ልጄ ሆይ! ለቅሶ የእርሱን (የአላህን) እዝነት ያስገኛል። ቀሪውን ሕይወትህን እያለቀስክ ማሳለፍ ከቻልክ አድርገው። በዚህ ምክኒያት አላህ ያዝንልህ ይሆናል።”
ኢብን አል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) ቀጣዩን አባባል በሐቅ ተናግረዋል፦ “ብልህ ሰው ማለት የቀልቡን እንጂ የአካሉን መሞት የማይፈራ የሆነ ነው።”
Forwarded from"ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል"{وإلى ربك فارغب}✍🏻𝐬𝐮𝐦𝐞𝐲𝐚

October 20, 2026 97