የዱንያ እውነታ
ይህች አለም አላህ ሊፈትነንና ሊሞክረን የሰራት ጊዜያዊ ማረፊያ እንጂ የዘላለም መኖሪያችን አይደለችም። ከህፃንነት እስከ እርጅና ከፅንስ እስከ መቃብር ያለው የህይወት ሂደታችን በቅጽበት እንደምትነፍስ ነፋስ ፈጣን ነው። እስኪ አስተውል የህይወታችን የልብ ምትና የአተነፋፈሳችን ቁጥር ሙሉ በሙሉ በአላህ ችሎታና እጅ ስር ያለ ሆኖ ሳለ በዱንያ ውበትና በጊዜያዊ ጥቅም ተታለን ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትን ታላቅ ቀን እንዴት እንረሳዋለን? አላህ በቁርዓኑ
«إنَّ إلَى رَبِّكَ الرُّجْعَى»
(በእርግጥ ወደ ጌታህ መመለስ አለ)
ሲል ያስጠነቀቀን የትም ብንሄድና ምንም ያህል ብንኖር የመጨረሻ መዳረሻችን እሱ ዘንድ መሆኑን ልባችን እንዲያውቀውና እንዲነቃ ነው።
ስለሆነም ከዚህ ታላቅ ማሳሰቢያ የምንወስደው ትምህርት የሞት ጥሪ ሳይመጣ ። ሰዓታችን ሳይጠናቀቅ ዛሬውኑ ወደ አላህ በመመለስ ታላቁን ስንቅ ልንይዝ ይገባል። ትዕቢትንና የአለምን አላፊ ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ልባችንን በተውሂድና በአላህ ፍርሃት፣ እጃችንን ደግሞ በመልካም ስራ እና በቅንነት ልናስጌጠው ይገባል።
እናም ወደ አላህ መመለስን ለነገ አንበል! ምክንያቱም የመጨረሻዋ ቀን መቼ እንደምትወጣ የምናውቀው ነገር የለምና , ከጌታችን ጋር ያለንን ግንኙነት በተውበት እና በመልካም ስነ ምግባር እናድስ
Forwarded from"ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል"{وإلى ربك فارغب}✍🏻𝐬𝐮𝐦𝐞𝐲𝐚

1October 15, 2026 117