قُلْ إِنَّ الْأَمْرَ كُلَّهُ لِلَّهِ በላቸው፡- ነገሩ ሁሉ የአሏህ ነው ! በዚህ ህይወት…

قُلْ إِنَّ الْأَمْرَ كُلَّهُ لِلَّهِ

በላቸው፡- ነገሩ ሁሉ የአሏህ ነው !

በዚህ ህይወት ውስጥ በሚያጋጥሙህ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች መካከል ቀልብህን እረፍት የሚሰጥ ታላቅ  ሀቅ አለ እርሱም ''ነገሩ ሁሉ የኣላህ ነው '' የሚለው የአሏህ ቃል ነው። በህይወትህ የምታልፍባቸው ውሳኔዎች ጭንቀቶች የምትመኛቸው መልካም ነገሮች እና እንዲወገዱልህ የምትፈልጋቸው መከራዎች በሙሉ በሰው ልጆች እጅ ሳይሆን በአሏህ ጥበብና ኃይል ስር ናቸው። ይህን እውነታ የተረዳ ልብ በጭራሽ ተስፋ አይቆርጥም ! ምክንያቱም ይህን ዓለም የሚመራውና የሚያስተናግደው ጌታ ከሁሉም ታላቅ ሰለሆነ ።

አሏህ ከእናቶች ይልቅ አዛኝና ሩህሩህ ነው ። ስለሆነም ነገሮች ሁሉ አንተ በፈለከው መንገድ ባይሄዱ እንኳ በፍጹም አትዘን! ምክንያቱም የአላህ ውሳኔ ሁልጊዜም ቢሆን ላንተ ከምትመኘው በላይ የተሻለና በኸይር የተሞላ ነው። ሕይወትህን  በሙሉ ለጌታህ ውክልና  ስጥ ! ልብህን ከሰዎች ጥገኛነት ነፃ አውጣ ። ልብህን በአሏህ ጥበብ ላይ ሙሉ በሙሉ አስመካት ። ነገሩ ሁሉ ከአሏህ ከሆነ የጥሩውም ሆነ የፈታኙ ነገር ፍጻሜው ላንተ መልካም ነው።  ስለዚህ ቀና በል ! አትጨነቅ አሏህ አለህ !!  ብቻ መልካም ሰራ እንጂ አሏህ አንተ ካቀድኸው እቅድ በላይ እጅግ ውብ አድርጎ ይክስሀል ።  ታገስ/ሺ !!!
October 11, 2026 108