የስራ መዝገቡ ላይ እጅግ የበዛ እስቲግፋርን ማኖር የቻለ ሰው ምንኛ ታደለ እሺ ለምታውቀው ወንጀልህ አላህን…

የስራ መዝገቡ ላይ እጅግ የበዛ እስቲግፋርን ማኖር የቻለ ሰው ምንኛ ታደለ

እሺ ለምታውቀው ወንጀልህ አላህን ምህረት ጠየቅክ ለማታውቀውስ?

ላስታወስከው ወንጀልህ ይቅርታን ጠየቅክ ለረሳከውስ?

ለትላልቅ ወንጀልህ ተውበት አደረክ ለትናንሹስ?

ለዚህ እኮ ነው አንደበት ከእስቲግፋር መቆጠብ የለበትም ሚባለው ለዚህ እኮ ነው አንድ ሙስሊም በራሱ ላይ ግዴታ ያደረገው የእስቲግፋር ዊርድ (ቋሚ ፕሮግራም) ሊኖረው ይገባል ሚባለው የሰው ልጅ በተሳሳችነቱ በአጥፊነቱ ልክ ምህረትን ጠያቂ ሊሆን ይገባዋል
October 3, 2026 128