Anthropic የ-AI ሲስተሞች ሮቦቶችን እና የላቦራቶሪ እቃዎችን በአንድ ወጥ መንገድ እንዲቆጣጠሩ… — Addis Intelligence — TG.ME

🤶 Anthropic የ-AI ሲስተሞች ሮቦቶችን እና የላቦራቶሪ እቃዎችን በአንድ ወጥ መንገድ እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል MHS የተሰኘ አዲስ ስታንዳርድ ይፋ አደረገ

➡️Anthropic እንደ Claude ያሉ የ-AI ሞዴሎች የተለያዩ የላቦራቶሪ እና የፋብሪካ መሳሪያዎችን በአንድ  Single interface እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል Model Hardware Standard (MHS) የተሰኘ ክፍት ስታንዳርድ ይፋ አድርጓል። ከዚህ ቀደም ለእያንዳንዱ መሳሪያ የተናጠል የፕሮግራሚንግ በይነገጾችን (APIs) መጠቀም ይጠይቅ የነበረውን አሰራር በማስቀረት MHS የትዕዛዝ የባህሪያት እና የደህንነት ገደቦችን በአንድ ወጥ ድራይቨሮች እንዲያስተዳድሩ ያደርጋል።

➡️ይህ አሰራር የ-AI ኤጀንቶች የትዕዛዝ መስመሮችን (CLI) ወይም ብጁ ኮዶችን በመጠቀም ከመሳሪያዎች ጋር እንዲገናኙ ስራዎችን እንዲመሩ እና በሙከራ ውጤቶች ላይ ተመስርተው አሰራራቸውን እንዲያስተካክሉ ያስችላቸዋል። Anthropic እንዳስታወቀው አዲሱ ስታንዳርድ የተለያዩ መሳሪያዎችን ወደ ላቦራቶሪ ወይም ፋብሪካ የማካተት እና የማዋሃድ ጊዜን ከሳምንታት ወደ ጥቂት ሰዓታት አልፎ ተርፎም ደቂቃዎች ዝቅ አድርጎታል።

🤩 @AddisIntel
👍1
August 28, 2026 118