Claude የተለያዩ አካላዊ የሳይንስ መሳሪያዎችን በራሱ እንዲያንቀሳቅስ በተደረገበት የሙከራ ሂደት እጅግ አስደናቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በ QuEra የኳንተም ኮምፒውተር ሌሰሮችን የማስተካከል ስራ ላይ ባለሙያዎች ከ5 እስከ 10 ደቂቃ የሚፈጅባቸውን ተግባር Claude ያለ ሰው ቁጥጥር በ6 ሰከንዶች ውስጥ ያጠናቀቀ ሲሆን የስኬት ምጣኔውንም ከ 58% ወደ 99.3% አሳድጎታል።
በተጨማሪም በ Genentech የፈሳሽ መመጠኛ መሳሪያዎችን (Pipetting) በራሱ እንዲያስተካክል የተደረገ ሲሆን በአንድ ዩኒቨርሲቲ ላቦራቶሪ ደግሞ ሌሊት በሰው እጅ የሚከናወነውን ስራ ሙሉ በሙሉ በራሱ አከናውኗል። በካሊፎርኒያ ወንዝ ውስጥ የሚገኝ የፍሳሽ ብክለትን ለመለየት የተደረገውን የ qPCR ምርመራ በተሳካ ሁኔታ የመራው Claude ሳይንሳዊ ላቦራቶሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አውቶሜሽን እየተሸጋገሩ መሆናቸውን አሳይቷል።
