አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ፊት በመመልከት ብቻ የስኳር እና የደም ግፊት በሽታዎችን መለየት የሚያስችል… — Addis Intelligence — TG.ME

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሰዎችን ፊት በመመልከት ብቻ የስኳር እና የደም ግፊት በሽታዎችን መለየት የሚያስችል አቅም አገኘ በቶኪዮ የሚገኙ ተመራማሪዎች በጥቂት ሰከንዶች የፊት ቪዲዮ አማካኝነት የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ምልክቶችን በከፍተኛ ትክክለኛነት መለየት የሚችል አዲስ የ AI ሲስተም ይፋ አድርገዋል። ቴክኖሎጂው በሰው ዓይን የማይታዩ ጥቃቅን የደም ዝውውር ለውጦችን የልብ ምት ቅጦችን እና የቆዳ ቀለም ልዩነቶችን በመተንተን ነው በሽታዎቹን የሚለየው። 🖱️ የደም ግፊትን በ30 ሰከንዶች ቪዲዮ በ 95% እንዲሁም በ 5 ሰከንዶች ብቻ በ 90.3% ትክክለኛነት ለይቷል 🖱️ የስኳር በሽታን በ30 ሰከንዶች ቅጂ በ 88.2% እንዲሁም በ 5 ሰከንዶች ውስጥ በ 81.2% ትክክለኛነት መለየት ችሏል 🖱️ የደም ግፊት መለኪያ ማሰሪያ (Cuff) ሳይጠቀም የደም ግፊትን በከፍተኛ ትክክለኛነት መገመት የቻለ ሲሆን አማካይ የስህተት መጠኑ -2.6 mmHg ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል ምንም እንኳን ቴክኖሎጂው በአሁኑ ወቅት መደበኛውን የደም ምርመራ ሙሉ በሙሉ ባይተካም ወደፊት ተራ ካሜራዎችን ብቻ በመጠቀም የጤና እክሎችን አስቀድሞ ለመለየት ትልቅ ተስፋ የጣለ ግኝት ነው። 🤩  @AddisIntel

August 31, 2026 98 1