AI የህጻናት የቅርብ ጓደኛ እየሆነ መምጣቱ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ስጋት ፈጥሯል ታዋቂው የማህበራዊ ሳይኮሎጂ… — Addis Intelligence — TG.ME

‼️ AI የህጻናት የቅርብ ጓደኛ እየሆነ መምጣቱ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ስጋት ፈጥሯል

ታዋቂው የማህበራዊ ሳይኮሎጂ ባለሙያ ጆናታን ሃይድት  እንዳስጠነቀቀው ማህበራዊ ሚዲያዎች የልጆችን ትኩረት የመሰብሰብ አቅም ያዛቡትን ያህል የ AI አጋሮች ደግሞ የልጆችን ጥልቅ ስሜታዊ ትስስር የመቆጣጠር አደጋ አላቸው። ፈጽሞ የማይደክመው የማይፈርድበት እና ልጅ በሚፈልገው መንገድ ብቻ ምላሽ የሚሰጠው የ AI ጓደኛ ከእውነተኛ ሰዎች ጋር ከሚደረግ ማህበራዊ ግንኙነት ይልቅ ለህጻናት ይበልጥ ሳቢ እየሆነ መጥቷል።

🔺ህጻናት ከወላጆቻቸው ከቤተሰቦቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ይልቅ ከ AI ጋር ጠንካራ ስሜታዊ ትስስር  የመፍጠር ስጋት ተደቅኗል

🔺 የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትርፍ ለማግኘት ሲሉ እነዚህን የልጆች “ምርጥ ጓደኞች” ዳታ መሰብሰቢያ ማስታወቂያ ማሰራጫ እና የተጠቃሚውን ትኩረት መቆጣጠሪያ ሊያደርጓቸው ይችላሉ

🔺 የመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ህጻናት ከ AI አጋሮች ጋር ባልተገባ መልኩ እየተቆራኙ እና ከእውነተኛው ዓለም ማህበራዊ ግንኙነት እየራቁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል

🤩 @AddisIntel
👍3
September 1, 2026 38