እግዚአብሔር በህይወትህ ላይ የተናገረው ቃል አሁንም ህያው ነው።
አሁንም የጸና ነው።
አሁንም አዎ ነው።
እግዚአብሔር ቃል ገብተው ጥለውህ እንደሄዱ ሰዎች አይደለም። በውሸት ቃል አይገባም (አያታልልም) የዘኁልቁ መጽሐፍ 23፥19 ይህንን ሙሉ በሙሉ ይቋጨዋል፦👇
እግዚአብሔር ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም ፣ ተናግሯል እርሱም ያደርገዋል። ቃል ገብቷል እርሱም ዳር ያደርሰዋል።
እርሱ የገባው ተስፋ ሁሉ በክርስቶስ አዎ እና አሜን ነው።
ፈውስ ፣
ነፃነት ፣
ተሃድሶ . . . . . . .
ከወራት ወይም ከዓመታት በፊት በህይወትህ ላይ የተናገረው ቃል።
ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ጊዜው አላለፈበትም። አንዱም አልተሰረዘም። ከእነዚህ ውስጥ አንዱም ቢሆን አንተ ይገባሃል ለማለት በሚያስችልህ የራስህ ፍጹምነት ላይ የተመሰረተ አልነበረም።
ጠላት የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት የሚያምን አማኝ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህም ነው ዋነኛ ስልቱ የእግዚአብሔርን ቃል (ቅዱሳት መጻሕፍትን) ሙሉ በሙሉ እንድትክድ ማድረግ ሳይሆን ፣ ቃሉ አሁን ላለህበት የተለየ ሁኔታ እንደማይሰራ እንድታምን ማድረግ የሆነው።
በዚህ አትታለል ፣ እግዚአብሔር የገባልህን ተስፋ አልረሳውም።
እርሱ ተናግሯል ፣ እርሱ ያደርገዋል ፣ እርሱ ይፈጽመዋል።
አሜን ነው ወገኖች !













